የ HTML elements:
HTML በ elements የተዋቀረ ነው። የሚከተሉት elements የ HTML ናቸው።
headings,
paragraphs,
links,
buttons,
forms,
lists...
ጥቂቶቹ ናቸው።
እስኪ የHTML elementsን ጥቅም በትንሹ እንይ። የHTML elements በቁጥር ብዙ እንደመሆናቸው፣ ጥቅማቸውም በዛው ልክ የትዬለሌ ነው!
የኤለመንቶችን ጥቅም እስኪ በትንሹ እንዘርዝር።
Headings: የምንጽፋቸውን ጽሁፎች ርዕስ በርዕስ ከፋፍሎ ለማስቀመጥ ይረዳናል።
Ordered lists and unordered lists: የሚዘረዘሩ ነገሮችን በቁጥር ወይም በ boolits ለማስቀመጥ ያገለግለናል።
Links: አንድን web page ወይም file ለማገናኘት ይጠቅመናል
Form: የተለያዩ መጠይቆችን ስናዘጋጅ የሚያገለግለን element ነው።
በዚህ ክፍል እንዴት አድርገን ሄዲንግ (heading) ፓራግራፍ፣ (paragraph) እና አዲስ መስመር (new line) እንደምንሰራ እናያለን።
learn how to create elements
How to create elements:
HTML የሚሰራው ኤለመንቶቹን ታግ በማድረግ ነው። ታግ ማድረግ ማለት ለምሳሌ፣ ሳንድዊች የሚሰራው እንቁላልን በሁለት ዳቦዎች በማጣበቅ ነው። ስለዚህ እንቁላሉ በሁለቱ ዳቦዎች ታግ ተደርጓል ለማለት እንችላለን።
ባጠቃላይ፣ ሁልጊዜም የHTML elements ሲጻፉ፣ በ "<>" እና "< / >" ታግ ይደረጋሉ።
የHTML code ለመጻፍ ምንም የተለየ software install ማድረግ አይጠበቅብንም። ኮምፒውተራችን ላይ ተጭኖ የመጣውን "Notepad" ተጠቅመን የHTML code መጻፍ እንችላለን።
አሁን አንድ heading እንስራ።
Learn how to creating headings now
Steps for creating headings:
በHTML 6 heading levels አሉ። "heading level 1" ማለት የጽሁፋችን ዋና ርዕስ የሚቀመጥበት ሲሆን፣ "heading level 2, 3, 4, 5, & 6" ደግሞ ጽሁፋችን ላይ የሚገኙ ንኡስ ርዕሶች እንደየደረጃቸው የሚቀመጡበት ነው.
በመጀመሪያ፣ "Notepad"እንከፍትና edit box ሲመጣልን የሚከተለውን ኮድ በጥንቃቄ እንጽፋለን።
<!DOCTYPE html>
<head>
<HTML>
<title>My first web page</title>
</head>
<body>
<h1>This is the first heading level 1.</h1>
</body>
</html>
እነዚህ ከላይ የተጻፉት ኮዶች የ simple web page ከሞላ ጎደል full structure ነው።
check our first web page (for screen reader users)
እስኪ ከመጀመሪያው መስመር ጀምሮ የተጻፉትን ኮዶች አንድ በአንድ እንያቸው።
1. <!DOCTYPE html>
ይህ ኮድ ማንኛውንም HTML file መጻፍ ስንጀምር ግዴታ የምናስገባው ኮድ ነው። web developers እንደሚሉት፣ ከላይ የተጻፈውን ኮድ መጻፍ የተጀመረው፣ HTML ወደ version five ሲያድግ ነው።
ይህንን ኮድ መጀመሪያ ላይ ጻፍን ማለት፣ ለብራውዘራችን የምንጽፈው የ HTML file base ያደረገው፣ በ HTML 5 እንደሆነ እየነገርነው ነው ማለት ነው።
2. <html>
ይህ ደግሞ፣ HTML የሚባል element እየከፈተልን ነው። ከዚህ በኋላ የምንጽፈው ጽሁፍ በሙሉ HTML በሚባለው element ውስጥ እንደሚሆን እንወቅ።
3. <head>
ይህ ኮድ ደግሞ፣ head የሚባል element እየከፈተልን ነው። HTML ላይ የሚጻፉ ጽሁፎች በሁለት ይከፈላሉ።
የመጀመሪያው Head ሲባል፣
የመጨረሻው ደግሞ፣ Body ይባላል።
Head የተለያዩ መረጃዎችን ቢይዝም፣ ለዚህ ቲቶር ግን፣ የጽሁፋችን ርዕስ እንደሚቀመጥበት ማወቃችን ብቻ በቂ ነው። በሌላ ጊዜ ስለ CSS ስንማር detail እናያለን።
4. <title>
ይህ ደግሞ የጽሁፉን ዋና ርዕስ ለማስገባት ስንፈልግ የምንጽፈው ኮድ ነው። እኔ ከላይ የጻፍኩትን ምሳሌ ብንወስድ፣ <title> ካልኩ በኋላ፣ My first web page/title> ብዬ ጽፊያለሁ። ይህም ማለት፣ የዕኔ ጽሁፍ ርዕሱ፣ My first web page ነው ማለት ነው።
6.</head>
ይህ ደግሞ፣ በፊት ከፍተነው የነበረውን Head የተባለውን element ይዘጋልናል።
7.<body>
ይህ ኮድ ደግሞ Body የተባለ element ይከፍታል።
8.<h1>This is the first Heading level 1.</h1>
ይህ ደግሞ፣ This is the first Heading level 1. Heading level 1 ላይ ያስቀምጠዋል ማለት ነው።
አሁን ያየነው Heading level one እንዴት እንደሚሰራ ነው። ታዲያ፣ ከ Heading level 2 እስከ Heading level 6 እንዴት ነው የምንሰራው? ይህ የዕናንተ የቤት ስራ ይሁን።
learn how to create paragraph now
How to create paragraphs:
አንድን paragraph ለመጻፍ፣<p> እና</p> እንጠቀማለን።
እስኪ ይህንን ኮድ ተጠቅመን አንድ Paragraph እንጻፍ። የምንጽፈው paragraph HTML stands for 'Hyper text markup language'. ስለዚህ፣ የparagraph element እንክፈት።<p>
ከዛም፣ HTML stands for Hyper text markup language. ብለን እንጽፋለን።
በመጨረሻም፣ ፓራግራፉን እንዘጋዋለን። </p>
Done! አንድ paragraph ጻፍን! (party)(party)(party)
Check our progress! (for screen reader users.)
Next: learn How to create new line
How to insert new line in HTML:
አዲስ መስመር ለመጀመር፣ <br> ነው የምንጠቀመው።
<br> closing tag የለውም።
በመጨረሻም፣ እስካሁን የጻፍናቸውን ኮዶች save ማድረግ አለብን። እንደምታውቁት፣ notepad የምንጽፋቸውን ፋይሎች save የሚያደርገው፣ በ.txt ነው። ነገር ግን፣ እኛ የምንፈልገው፣ በ .HTML file extention save እንዲሆንልን ነው።
ይህንን ማድረግ ቀላል ነው! save ስናደርግ File name ይጠይቀናል። by default ራሱ የሆነ ስም ይሰጠዋል። እኛም፣ by default የተሰጠውን ስም አጥፍተን የራሳችንን ስም እንሰጠዋለን። ለምሳሌ፣ "My first HTML practice.HTML"
ይህንን ጽፌ "save" በምልበት ጊዜ፣ ፋይሉ በ HTML extention save ይሆናል።
አስታውሱ! File name በምትሰጡበት ጊዜ የሚከተሉትን ነገሮች አትርሱ።
save በምታደርጉበት ጊዜ፣ ኮምፒውተራቹህ የሰጠውን default file name ማስወገዳችሁን አስቀድሙ
የራሳችሁን file name መጻፍ ስትጀምሩ quote (") በመክፈት ጀምሩ።
file ስማቹህ መጨረሻ ላይ .HTML የሚል መጻፍ አለበት።
በመጨረሻም፣ quote (") መዝጋታችሁን አትርሱ።
በቀጣይ ክፍል እንገናኝ!
Go to part two now!